ይህን ለሚያዩ ሁሉ ሰላም ይሁን!

Tuesday, July 19, 2011

የእለት እንጀራ

መዝሙር 23

1 እግዚአብሔር እረኛዬ ነው፥ የሚያሳጣኝም የለም።
2 በለመለመ መስክ ያሳድረኛል፤ በዕረፍት ውኃ ዘንድ ይመራኛል።
3 ነፍሴን መለሳት፥ ስለ ስሙም በጽድቅ መንገድ መራኝ።
4 በሞት ጥላ መካከል እንኳ ብሄድ አንተ ከእኔ ጋር ነህና ክፉን አልፈራም፤ በትርህና ምርኵዝህ እነርሱ ያጸናኑኛል።
5 በፊቴ ገበታን አዘጋጀህልኝ በጠላቶቼ ፊት ለፊት ራሴን በዘይት ቀባህ፥ ጽዋዬም የተረፈ ነው።
6 ቸርነትህና ምሕረትህ በሕይወቴ ዘመን ሁሉ ይከተሉኛል፥ በእግዚአሔርም ቤት ለዘላለም እኖራለሁ።

2 comments:

  1. እንዴት ነህ በአያሌው፡፡ ይህንን ጸሎት በቃልህ አጥናና ጸልየው ብላ የመከረችኝ አንዲት መንፈሳዊ እህቴ ነበረች፡፡ እርሷ ተጠቅማበት እንደሆነ እርግጠኛ ነኝ፡፡ እኔ ግን ገና ላጠናው ስሞክር..አንድ ሺ ጥያቄዎች ይመጡብኛል፡፡ እረኛ? ያሰማራኛል?...አረ በለው! እልና እተወዋለሁ፡፡ ምክንያቱም፤ ራሴን ሳየው እና ስመረምረው፤ በምንም መመዘኛ እግዚአብሔር ያሰማራኝ እና ያገደኝም በግ አልመስልምና፡፡ አንተስ? ራስህን ከጸሎቱ አንጻር እንዴት ታየዋለህ፡፡ እስቲ ጻፍ፡፡ ...በነገራችን ላይ ማራናታ፤ እኔ ብሎግ ላይ የምትጽፈውን ኮሜንት ያህል እንኳን ራስህ ብሎግ ላይ ስትጽፍ ስለማላይህ ሁሌ እናደድብሃለሁ፡፡ ብዙ የምትጽፈው እና ማለት የምትፈልገው ነገር እንዳለህ እረዳለሁና፡፡ ስምህንም ማራናታ ያልከው ለዚህ መሰለኝ፡፡ ስለዚህ ጻፍ! ብዬ አዝሃለሁ፡፡ ሁለተኛ ደግሞ የyahoo ኢሜልህን ቼክ አድርግ፤ እኔ አዲስ ነገር ስለጥፍ ከማሳውቃቸው ሰዎች ዝርዝር ውስጥ አስገብቼሃለሁና፡፡ነጋቲ ቡላ!

    ReplyDelete
  2. የእግዜር ሰላምታ ናዖድ!
    እኔ በጣም ደኽና ነኝ ይመስገነው!
    "...ራሴን ሳየው እና ስመረምረው፤ በምንም መመዘኛ እግዚአብሔር ያሰማራኝ እና ያገደኝም በግ አልመስልምና.." በፈገግታ ነው ይነበብኩት:: አንተስ ብለህ ጭራሽ ባልጠበቁት ጥያቄ አፋጠጥቀኝ:: እንዲሁ ለምስጋና ባጋጣሚዎች አነበንበዋለሁ::
    "እግዚአብሔር እረኛዬ ነው፥ የሚያሳጣኝም የለም። በለመለመ መስክ ያሳድረኛል፤ በዕረፍት ውኃ ዘንድ ይመራኛል።" የሚለው የተለየ ስሜት ይሰጠኛል::

    ቀሪዉን በኢሜልህ ምላሽ ልኪያለሁ

    ReplyDelete