ይህን ለሚያዩ ሁሉ ሰላም ይሁን!

Thursday, December 2, 2010

 " እንግዲህ ሌሎች እንዲያደርጉላችሁ የምትፈልጉትን ነገር እናንተም ለእነርሱ እንዲሁ አድርጉላቸው፣ የሕግና የነቢያት ትምህርትም የሚሉት ይህንኑ ነው፡ በጠበበው በር ግቡ፤ ወደ ጥፋት የሚያስገባው በር ሰፊ፥ መንገዱም ትልቅ ነውና፥ ወደዚያ የሚገቡትም ሰዎች ብዙዎች ናቸው፡፡ ነገር ግን ወደ ሕይወት የሚያደርሰው መንገድ ቀጭን፣ በሩም የጠበበ ነው፣ ይህን የሚያገኙት ጥቂቶች ናቸው። ከሐሰተኞች ነቢያት ተጠንቀቁ፣ እነርሱ የበግ ለምድ ለብሰው በመካከላችሁ ይመጣሉ፣ ግን በውስጣቸው ነጣቂ ተኵላዎች ናቸው። ፍሬያቸውም አይታችሁ እነርሱን ታውቋቸዋላችሁ፣ ከእሾኽ ቊጥቋጦ የወይን ፍሬ፣ ከኵርንችትስ በለስ ይለቀማልን? እንዲሁ መልካም ዛፍ ሁሉ መልካም ፍሬ ያፈራል፣ ነገር ግን መጥፎ ዛፍ መጥፎ ፍሬ ያፈራል፡፡ መልካም ዛፍ መጥፎ ፍሬ ማፍራት አይችልም፣ መጥፎ ዛፍም መልካም ፍሬ ማፍራት አይችልም፡፡ መልካም ፍሬ የማያፈራ ዛፍ ሁሉ ይቆረጣል፣ ወደ እሳትም ይጣላል።"

No comments:

Post a Comment