ይህን ለሚያዩ ሁሉ ሰላም ይሁን!

Friday, April 13, 2012

ትንቢተ ኢሳይያስ ምዕራፍ 53።

1፤ የሰማነውን ነገር ማን አምኖአል? የእግዚአብሔርስ ክንድ ለማን ተገልጦአል?
2፤ በፊቱ እንደ ቡቃያ ከደረቅም መሬት እንደ ሥር አድጎአል። መልክና ውበት የለውም፥ ባየነውም ጊዜ እንወድደው ዘንድ ደም ግባት የለውም።
3፤ የተናቀ ከሰውም የተጠላ፥ የሕማም ሰው ደዌንም የሚያውቅ ነው፤ ሰውም ፊቱን እንደሚሰውርበት የተናቀ ነው፥ እኛም አላከበርነውም።
4፤ በእውነት ደዌያችንን ተቀበለ ሕመማችንንም ተሸክሞአል፤ እኛ ግን እንደ ተመታ በእግዚአብሔርም እንደ ተቀሠፈ እንደ ተቸገረም ቈጠርነው።
5፤ እርሱ ግን ስለ መተላለፋችን ቈሰለ፥ ስለ በደላችንም ደቀቀ፤ የደኅንነታችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ ነበረ፥ በእርሱም ቍስል እኛ ተፈወስን።
6፤ እኛ ሁላችን እንደ በጎች ተቅበዝብዘን ጠፋን፤ ከእኛ እያንዳንዱ ወደ ገዛ መንገዱ አዘነበለ፤ እግዚአብሔርም የሁላችንን በደል በእርሱ ላይ አኖረ።
7፤ ተጨነቀ ተሣቀየም አፉንም አልከፈተም፤ ለመታረድ እንደሚነዳ ጠቦት፥ በሸላቶቹም ፊት ዝም እንደሚል በግ፥ እንዲሁ አፉን አልከፈተም።
8፤ በማስጨነቅና በፍርድ ተወሰደ፤ ስለ ሕዝቤ ኃጢአት ተመትቶ ከሕያዋን ምድር እንደ ተወገደ ከትውልዱ ማን አስተዋለ?
9፤ ከክፉዎችም ጋር መቃብሩን አደረጉ፥ ከባለጠጎችም ጋር በሞቱ ሆኖም ግፍን አላደረገም ነበር፥ በአፉም ተንኮል አልተገንበትም ነበር።
10፤ እግዚአብሔርም በደዌ ያደቅቀው ዘንድ ፈ  ደ፤ ነፍሱን ስለ ኃጢአት መሥዋዕት ካደረገ በኋላ ዘሩን ያያል፥ ዕድሜውም ይረዝማል፥ የእግዚአብሔርም ፈቃድ በእጁ ይከናወናል።
11፤ ከነፍሱ ድካም ብርሃን ያያል ደስም ይለዋል፤ ጻድቅ ባሪያዬም በእውቀቱ ብዙ ሰዎችን ያጸድቃል፥ ኃጢአታቸውን ይሰከማል።
12፤ ስለዚህም እርሱ ብዙዎችን ይወርሳል፥ ከኃያላንም ጋር ምርኮን ይከፋፈላል፤ ነፍሱን ለሞት አሳልፎ ሰጥቶአልና፥ ከዓመፀኞችም ጋር ተቈጥሮአልና፤ እርሱ ግን የብዙ ሰዎችን ኃጢአት ተሸከመ፥ ስለ ዓመፀኞችም ማለደ።

Tuesday, July 19, 2011

የእለት እንጀራ

መዝሙር 23

1 እግዚአብሔር እረኛዬ ነው፥ የሚያሳጣኝም የለም።
2 በለመለመ መስክ ያሳድረኛል፤ በዕረፍት ውኃ ዘንድ ይመራኛል።
3 ነፍሴን መለሳት፥ ስለ ስሙም በጽድቅ መንገድ መራኝ።
4 በሞት ጥላ መካከል እንኳ ብሄድ አንተ ከእኔ ጋር ነህና ክፉን አልፈራም፤ በትርህና ምርኵዝህ እነርሱ ያጸናኑኛል።
5 በፊቴ ገበታን አዘጋጀህልኝ በጠላቶቼ ፊት ለፊት ራሴን በዘይት ቀባህ፥ ጽዋዬም የተረፈ ነው።
6 ቸርነትህና ምሕረትህ በሕይወቴ ዘመን ሁሉ ይከተሉኛል፥ በእግዚአሔርም ቤት ለዘላለም እኖራለሁ።

Saturday, December 11, 2010

ድቀተ ልቦና

 
ሰው ልቦናውን ካጣ ደግነትን ይቅር ባይነትን ቅንነትን እና ትእግስትን ገንዘቡ ማድረግ ይሳነዋል::  እንኪያስ እንግዲህ ልቦና የሕይወት መሰረት ነው ::  ጠቢቡም በመጽሃፉ ይህን ሲመሰክር እንዲህ ብሎታል: "አጥብቀህ ልብህን ጠብቅ፥ የሕይወት መውጫ ከእርሱ ነውና።" ምሳሌ4:23

ለድቀተ ልቦና ወይም የልቦና መውደቅ መንስኤ የሚሆነው በሀጥያት መኖር ነው:: በሀጥያት የሚኖር ሰው በፈቃዱ ከፈጣሪው ጋር ያለዉን ሕብረት ያደፈርሳል:: የሀጥያት ደሞዝ ደግሞ ሞት ነው:: ስለዚህ በሞት ላለመኖር የሞትን መንስኤ (ሀጥያትን) ማወቅ እና ማስወገድ ያስፈልጋል ማለት ነው:: ምክንያቱም ለችግሮች ሁሉ ምፍትሄ መፈለግ የሚጀመረው ከችግሩ መንስኤ ነውና:: ለድቀተ ልቦና ምክንያት የሆነውን ሀጥያትን ምንጩን ማወቅና ማድረቅ የመፍትሄ መነሻ ይሆናል::

የሀጥያት ህልውና የሚጀምረው ሀጥያትን ከማወቅ ነው:: ስለዚህ ሀጥያትን አለማወቅ እንዴት ይቻላል? በግብጽ የሃይማኖት አባት አቡነ ሸኖዳ The release of th Spiritበሚል መጽሃፋቸው ላይ ስለ ሀጥያት እውቀት እንዲህ አስፍረውታል”…there is something else on earth which I think the spirit cannot be released from however it tries! .. To be released of this thing is a joy only to be attained in the eternity.. But what is this thing?It is the release from the knowledge of sin:”

ቀጥለውም ስለሀጥያት እውቀት አመጣጥ ሲገልጹ የሰው ልጅ ሲፈጠር ፍጹም በሆነ ንጽህና ስለሀጥያት ምንም ግንዛቤ ሳይኖረው እንደነበር እና ጥርጥሬን ውሸትን ህይዋን ባለማወቋ የሀጥያትእውቀት እንዴት እንደሰረጸ ሲግልጹ…….”He created him simple, pure, no knowledge of sin at all and not even the details or the names of sin.. That was before he ate from the tree of the knowledge of good and evil.. He was as innocent as a child and perhaps more. Therefore, when Eve was tempted by the serpent she had no knowledge. The serpent lied and said to her "You will not surely die" “..you will be like God" Gen. 3.-5 But as Eve knew nothing about lying she believed the serpent. She did not suspect the truth of its words because she knew nothing about doubt.”

እንግዲህ ሃጥያትን አለማወቅን ካልቻልን ሃጥያትን እያወቅን አለማድረግ ወይም ላደረግነው በደል ይቅርታን መጠየቅ እና እራሳችንን እንደገና ማደስ የችግሩ መፍትሄ ይሆናል:: በእውቀት ቅድስና ላይ መድረስ አይቻልም::  ቅድስና የምንኖረው እንጂ የምናውቀው እንደሆነ ሁሉ ከጥፋት ጎዳና ወደሂወት ጎዳና ልቦናችንን መመልስ መንፈሳዊነት ነው::

በጠማማ መንገድ የኖረን ልቦና መቀየር ደግሞ የእግዚያብሄር ፈቃድ ብቻ ነው:: እርሱ ወደርሱ የምታይን ነፍስ እና ጽድቅን የተራበች ልቦና አይተዋትም:: እግዚያብሄር እርሱን ከምትፈልግ ልቦና የንስሃ ፍሬን ይፈልጋል:: ያለትንሳኤ ልቦና (ንስሃ) ደግሞ ፍጹም የሆነን መንፈሳዊ ሰላም ማግኘት አይቻልም:: መጸጸት:ባደረግነው ሃጽያት በእግዚያብሄር ፊት ማፈር: ቂምን: በቀልን: ጥላቻን ሁሉ አስወግደን ትእቢት በሌለበትና በተሰበረ ልቦና የእግዚያብሄርን መሃሪነት እና ታጋሽነትን ብቻ የመንፃት ተስፋ አድርጎ በማመን እራስን ለንስሃ ማቅረብ ትሁትነት ነው:: ሓጽያትን አውቆ ንስሃ አለመግባት አንድም ትእቢት ነው አልያም የእግዚያብሄርን ይቅር ባይነት እና መሃሪነትን መጠራጠር ነው::ከሁለቱም ካልሆነ በሃጽያት ላይ እርም አለማለትን ያሳያል::

የምህረ: የፍቅር: የሰላም ሁሉ አለቃ አቤቱ እግዚያብሄር ሆይ የንስሃ ህይወትን እና እንደ ፈቃድህ መሄድን አስተምረን::